በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ትእዛዝ መሰረት
እንዲህም አላቸው፦ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ። — ማርቆስ 16፥15
የ አማኑኤል ሙሉወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ቅዱሳንና እንዲሁም ከተወደደ የጌታ ባሪያ ከወንድማችን ፓስተር ብርሃን ( Berhane Woldegebriel ) ጋር አብሮ በመሆን ፣ ድንቅ የሆነ የጎዳና የወንጌል ስርጭት ጊዜ ነበረን፣ ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን ከህፃን እስከ አዋቂ የተሳተፈበት ነበር! እነ ሆሊዬም አልቀሩ ከሁሉ የሚበልጠውን፣ ለሰው ልጆች ሁሉ የሚበጀውን ፣ ይህንን የዘለአለም ህይወት የሆነውን የምስራቹን ወንጌል መናገር ምንኛ ደስ ያሰኛል በእውነት በብዙ ደስታ ልባችን ሀሴት እያደረገ ነው የተመለስነው! የያዝነው እውነት ትልቅ ነው! ኢየሱስ አስተማማኝ የማያሳፍር ጌታ ነው!! ሰዎች ሁሉ ሊሰሙት የሚገባ! ከኅጢያት ባርነት ነፃ የሚያወጣ!! ከዘለአለም ሞት የሚያድን! ደዌን የሚፈውስ! እስራትን የሚበጣጥስ!! ቀንበርን የሚሰብር! በእውነት ይህንን የምስራች ወንጌል አለማብሰር ታዲያ ትልቅ በደል አይሆንምን የእኛ ድርሻ መናገር ነው የሚያድን እርሱ ነው!!የረዳን እግዚአብሔር ይመስገን ይህንን ይመስል ነበር